ስፓርት

ሲዳማ ቡና በኢትዮጵያ ዋንጫ ለፍጻሜ አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

April 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ሲዳማ ቡና መቻልን በመለያ ምት 7 ለ 6 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በፍፃሜው ከወላይታ ድቻ ጋር ይገናኛል፡፡

ወላይታ ድቻ ትናንት በግማሽ ፍፃሜው ሸገር ከተማን በማሸነፍ ለፍጻሜ መብቃቱ ይታወቃል፡፡

የዛሬው የሲዳማ ቡና እና መቻል ጨዋታ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ያለምንም ግብ ነበር የተጠናቀቀው፡፡

በኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን የሚሆነው ክለብ በቀጣዩ ዓመት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ተሳታፊ ይሆናል፡፡