Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ማንቼስተር ዩናይትድ ከበርማውዝ  ጋር አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት አጠናቅቋል፡፡

የበርንማውዝን ግብ  ሴሜኒዮ በመጀመሪያው አጋማሽ ሲያስቆጥር፤ ሆይሉንድ ማንቼስተር ዩናይትድን አቻ ያደረገች ግብ በጨዋታው መጠናቀቂያ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ በርንማውዝ በ50 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ማንቼስተር ዩናይትድ በ39 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ተጠባቂው የሊቨርፑል እና ቶተንሀም ሆትስፐር ጨዋታ በአንፊልድ ምሽት 12 ሠዓት ከ30 ይደረጋል፡፡

ከጨዋታው አስቀድሞ የሊቨርፑል ደጋፊዎች በአንፊልድ አካባቢ ደማቅ የድጋፍ እንቅስቃሴ እያሳዩ ነው፡፡

Exit mobile version