Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር የኢትዮጵያ ፖሊስ አትሌቶች ከ1 እስከ 3 በመያዝ አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በተጀመረው 5ኛው የምሥራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት ስፖርት ውድድር የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር የኢትዮጵያ ፖሊስ አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት በመውጣት አሸንፈዋል፡፡

በሌላ በኩል በወንዶች የአራት በ400 ሜትር የዱላ ቅብብል የኬኒያ ፖሊስ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ እና የታንዛንያ ፖሊስ ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል።

Exit mobile version