Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በ3ኛው የአፍሪካ-ኢራን ኢኮኖሚያዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በቴህራን እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የአፍሪካ-ኢራን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ጉባኤ እና በኢራን ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡
ጉባኤው በዋናነት በኢራን እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የኢንዱስትሪ፣ የንግድና የኢቨስትመንት ትስስር ለማጠናከር አተኩሮ የሚካሄድ ሲሆን፥ በኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሐሰን መሐመድ የተመራ የልዑካን ቡድን በመድረኩ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
የኢራን ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዝሽኪያን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ ሀገራቸው በጤና፣ በንግድ፣ በኢንዱስትሪና በግብርና ያስመዘገበችውን ስኬት በሚመለከት ልምድ፣ ተሞክሮና ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
በኢራንና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን በመጪው ዓመት ወደ 10 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ መታቀዱ ተገልጿል፡፡
ጉባኤው በነዳጅ፣ ፋርማሲውቲካል፣ በማዕድንና ማዕድን ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም በግብርና፣ ኢነርጂ፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ላይ አተኩሮ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
Exit mobile version