አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተደረገላቸው ድጋፍ ከ517 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ወደ ታዳጊና መካከለኛ ባለሃብትነት መሸጋገራቸውን የክልሉ ሥራና ስልጠና ቢሮ ገለፀ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አማረ አለሙ እንደገለፁት፤ ኢንተርፕራይዞቹ በተደረገላቸው የተጠናከረ የመንግስት ድጋፍ በየተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ውጤታማ ሆነዋል።
በዚህም ከ10 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል ፈጥረዋል ብለዋል።
በቀጣይም ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ፣ የመስሪያና የመሸጫ ቦታ በማመቻቸትና የገበያ ትስስር በመፍጠር ኢኮኖሚውን እንዲያነቃቁ እንደሚሰራ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የክልሉ 9ኛው የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር እና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ትርዒትና የደረጃ ሽግግር ሳምንት በኮምቦልቻ ከተማ መከፈቱ ይታወሳል፡፡