Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች በቴምር ምርት ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች በቴምር ምርት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች የከሊፋ ኢንተርናሽናል ቴምር አዋርድና የግብርና ኢኖቬሽን ዋና ጸሐፊ አብዱላሃብ ዘይድ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት÷ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)÷ የአዋሽ ተፋሰስ እና ቆላማ አካባቢዎች አፋር፣ ሶማሊያ፣ ጋምቤላ፣ ድሬዳዋ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችና በኦሮሚያ ክልል ጉጂና ቦረና ለቴምር ልማት ምቹ ሥነ-ምህዳር እንዳላቸው ጠቁመዋል።

በቴምር ምርት ልምድ ያካበቱ ድርጅቶችን ከተለያዩ ሀገራት በማሳተፍ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደረግበት የቴምር ፌስቲቫል በኢትዮጵያ ለማካሄድ በውይይ ላይ ከመግባባት ተደርሷል።

በፌስቲቫሉ የተሻሻሉ የቴምር ዝርያዎችና ቴክኖሎጂዎች፣ በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግና በአርሶአደሮች፣ አምራቾችና አቀናባባሪዎች መካከል ልምድ ልውውጥ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በቀጣይ የሚካሄደውን ፌስቲቫል ለማዘጋጀት ዝግጁ መሆኗን ሚኒስትሩ መግለፃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version