የሀገር ውስጥ ዜና

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎንደር አውሮፕላን ማረፊያ በራሱ ወጭ ለማከናወን ቃል ገባ

By Mikias Ayele

April 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ የጎንደር አውሮፕላን ማረፊያን ሙሉ ግንባታ በራሱ ወጭ ለማከናወን ቃል ገብቷል።

“ኑ ጎንደርን እንሞሽር” በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር  በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በጀት በመመደብ የጎንደር አውሮፕላን ማረፊያን ሙሉ ግንባታ እንደሚያከናውን ቃል ገብቷል።

ከዚህ በተጨማሪም የ5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ሥራ ለማከናወን አየር መንገዱ ቃል መግባቱን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ የሶማሌ ክልል 15 ሚሊየን ብር ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።