የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ክልል ካቢኔ የቀረበለትን የበጀት ክለሳ አፀደቀ

By Hailemaryam Tegegn

April 29, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የቀረበለትን የ214 ሚሊየን ብር የበጀት ክለሳ አፅድቋል።

የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ በክልሉ ተጨማሪ በጀት የጠየቁ ሥራዎች በመኖራቸው የበጀት ክለሳው ማስፈለጉ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት የፊዚካልና ፋይናንሻል አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ፕሮጀክቶችን በመለየት የላቀ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ላላቸውና የበጀት እጥረት ላጋጠማቸው ጉዳዮች ይውላል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ካቢኔው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ማስቀመጡን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡