የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለሥራ ጉብኝት ኮምቦልቻ ገቡ

By Yonas Getnet

April 29, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለሥራ ጉብኝት ኮምቦልቻ ከተማ ገብተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷የደጋጎቹና የትጉሃኑ ከተማ እንዲሁም የሀገራችን የኢንዱስትሪ ማዕከል የሆነችው ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ ገብተናል ብለዋል።

በቆይታቸውም በአካባቢው እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ አመልክተዋል፡፡

ኮምቦልቻ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸው የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የደቡብ ወሎ ዞንና የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ሃላፊዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡