Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 27ኛ መደበኛ ስብሰባ የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡

አዋጁ ወደ ሀገር የሚገቡና ከሀገር የሚወጡ እንስሳት እና የእንስሳት ምርቶች የዓለም የጤና ድርጅትን አሰራር እና ሕግ የተከተሉ እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል።

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥርም ነው የተመላከተው፡፡

አዋጁ ሀገር ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንድታጎለብት እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

በፍቅርተ ከበደ

Exit mobile version