አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የፌደራል ዋና ኦዲተር እና አልጀዚራ በኢትዮጵያ ከ15 ሺህ በላይ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አበርክተዋል።
ተቋማቱ በሕጻናት እና አዋቂዎች የሚነበቡ የተለያዩ ይዘት ያላቸው መጻሕፍትን ነው ያበረከቱት።
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መሰል ተግበራትን በማከናወን ማሕበራዊ ሃላፊነትን መወጣት ይገባል፡፡
ለቤተ መጻሕፍቱ ከተበረከቱት 15 ሺህ መጻሕፍት ውስጥ 10 ሺህ የሚሆኑት በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተበረከቱ ናቸው ተብሏል፡፡
ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ከዓለም አቀፍ የመጻሕፍት ቀን ወዲህ ከ20 ሺህ በላይ መጻሕፍት እንደተበረከቱለት ተመላክቷል፡፡
በዐምደወርቅ ሽባባው