አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ፒኤስጂ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ አርሰናልን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የፒኤስጂን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ ከመረብ አሳርፏል።
የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በቀጣይ ሳምንት ረቡዕ ምሽት በፓርክ ደ ፕሪንስ ስታዲየም ይደረጋል።
የመድፈኞቹ የቀድሞ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ኤሚሬትስ ስታዲየም ተገኝተው ጨዋታውን ተከታትለዋል