የሀገር ውስጥ ዜና

የስልጤ ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ10 ነጥብ 1 ሚለየን ብር ድጋፍ አደረጉ

By Tibebu Kebede

November 07, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ10 ነጥብ 1 ሚለየን ብር በላይ በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።

የስልጤ ዞን ነዋሪዎች ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት ለመግለፅና አሸባሪው ህወሓት ቡድንን ለማውገዝ ዞን አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

በዚሁ ወቅትም የዞኑ ነዋሪዎች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት 248 ሰንጋ በሬዎች፤ 17 ሙክት በግና ፍየል እንዲሁም 157 ሺ 2 መቶ ብር በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

የአይነት ድጋፉ በብር ሲተመን ከ10 ነጥብ 1ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን መገለፁን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!