የሀገር ውስጥ ዜና

የጠላት ሃይል ዙሪያውን በእሳት ቀለበት ተከቦ እየተመታ ነው – ዶ/ር አለሙ ስሜ

By Meseret Awoke

November 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የጠላት ሃይል ዙሪያውን በእሳት ቀለበት ተከቦ እየተመታ መሆኑን በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር አለሙ ስሜ ገለጹ።

ዶክተር አለሙ እንዳሉት ÷ አሸባሪው ህወሓት ከገባበት መውጫ አጥቶ በያለበት እንዲደመሰስ የተቀናጀ ዘመቻ እየተካሄደ ነው።

አሸባሪው ህወሓት በአማራና አፋር ክልሎች ወረራ ባደረገባቸው አካባቢዎች የሚያደርሰውን ጉዳት ለማስቆምና ቡድኑን ለማጥፋት የጸጥታ ሃይሉ የተቀናጀ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪው ÷ የሽብር ቡድኑና ተላላኪዎቹን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ለማጥፋት የተቀናጀ የአመራር ስምሪት መሰጠቱን ገልጸዋል።

በዚህም ከጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጀምሮ ሁሉም ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር መዝመታቸውን ተናግረዋል።

አሸባሪው ህወሓት በወረራ ከገባባቸው አካባቢዎች መውጫ አጥቶ በያለበት እንዲደመሰስ የተቀናጀ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር የዘመቱት የመከላከያ ሰራዊቱን ስራ ለመተካት ሳይሆን ህዝብን በማስተባበር የሽብር ቡድኑ በየትኛውም አካባቢ መውጫ እንዳያገኝና ተመልሶ ወደ ተንቤን በርሃ እንዳያመልጥ ለማድረግ መሆኑንም ዶክተር አለሙ ገልጸዋል።

አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት በኢትዮጵያ ላይ የሚመጣን ማንኛውም ጥቃት በብቃት በመመከት ጠላትን አሳፍሮ መመለስ የሚችል አቅም መፈጠሩንም አረጋግጠዋል።

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በበኩላቸው ÷ የጠላት ሃይል ዙሪያውን በእሳት ቀለበት ተከቦ እየተመታ መሆኑንም ገልጸዋል።

በዚህም ትግሉን በፍጥነት አጠናቆ ወደ ልማት መመለስ የሚያስችል የተደራጀና ራሱን ለመስዋዕትነት ያዘጋጀ የህዝብ ንቅናቄና አመራር መፈጠሩንም ተናግረዋል።

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጥሪ ተቀብለው ወደ ግንባር መዝመታቸውን ጠቅሰው ÷ ኢትዮጵያን ለማዳን በቂ ዝግጅት ተደርጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!