Fana: At a Speed of Life!

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር ለሕዳሴ ግድብ የ2 ነጥብ 7 ሚሊየን የጅቡቲ ፍራንክ ቦንድ ግዢ ፈጸመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የ2 ነጥብ 7 ሚሊየን የጅቡቲ ፍራንክ ቦንድ ግዢ ፈጽሟል፡፡ የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ አመራሮች በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በተገኙበት የቦንድ ግዢውን አስረክበዋል።…

የእናቶችና ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ የተጀመረው ሥራ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የእናቶችና ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ የጤና ሙያ ማህበራት የተጀመሩ ሥራዎችን እንዲያጠናክሩ የጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል። የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ማህበር 33ኛ ዓመታዊ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡ የጤና ሚኒስትር…

ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) አዲሱ ሊቀመንበር የኢጋድ የሚኒስትሮች…

በደንዲ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ደንዲ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ አደጋው ከግንደበረት ወረዳ ወደ ጊንጪ ከተማ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡ በደረሰው አደጋም የ6…

ኢፈ ቦሩ ት/ቤቶችን በተለያዩ ክልሎች የማስገንባቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – የኦሮሚያ ክልል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት የኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በተለያዩ ክልሎች በማስገንባት የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከርና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ሃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር)…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET-302 አደጋ ተጎጂዎች የመታሰቢያ ሃውልት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET-302 አደጋ ተጎጂዎች 6ኛ ዓመት የመታሰቢያ ሃውልት ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET-302 መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ኬንያ…

በአማራ ክልል 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017/18 የምርት ዘመን 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ መታቀዱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ÷በክልሉ…

የአሁኑ ትውልድ በክሕሎታችን ብቻ ኢትዮጵያን ማነጽ እንችላለን – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሁኑ ትውልድ የሕይወት መስዋዕትነት መክፈል ሳይጠበቅብን በክሕሎታችን ብቻ ኢትዮጵያን ማነጽ እንችላለን ሲሉ የሥራና ክሕሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀውን "ክህሎት ስለኢትዮጵያ" የፎቶግራፍ አውደ…

ቼልሲ ሌስተር ሲቲን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ሌስተር ሲቲን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ማርክ ኩኩሬላ በ60ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡…

397 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲና ኦማን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያና ኦማን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 397 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። 255 ወንዶች፣ 40 ሴቶች እና 18 ጨቅላ ሕጻናት በድምሩ 313 ኢትዮጵያውያን በተያዘው ሳምንት ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና…