Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ የሚከሰቱ ወረርሽኞችንና ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የሚከሰቱ ወረርሽኞችንና ድንገተኛ የጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገለጹ፡፡ በብራዛቪል ኮንጎ እየተካሄደ ያለው 74ኛው የአፍሪካ አህጉር የዓለም ጤና ድርጅት መድረክ…

10 ሺህ የዝንጀሮ ፈንጣጣ መከላከያ ክትባት ናይጄሪያ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 10 ሺህ የዝንጀሮ ፈንጣጣ መከላከያ ክትባት ናይጄሪያ ደረሰ። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የዓለም የጤና ስጋት መሆኑ ከተገለጸ ወዲህ ክትባቱን በመረከብ ናይጄሪያ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗ ተገልጿል። በዓለም የጤና ድርጅት የዓለም የጤና…

የወባ በሽታ ምልክቶችና መከላከያ መንገዶች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወባ በፕላዝሞዲየም ጥገኛ ተውሳኮች የሚመጣ አጣዳፊ የትኩሳት በሸታ ነው። የበሽታው ምልክቶች ከባድ ትኩሳት፣ ላብ፣ የሚያንዘፈዝፍ ብርድ ብርድ የሚል ስሜት፣ ራስ ምታት፣ የጡንቻ መጓጎል፣ ድካም፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ ተቅማጥና ትኩሳት፣ ብዙውን ጊዜ…

በሶማሌ ክልል የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል አበረታች ስራ መከናወኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ሆስፒታሎችን በሕክምና መሳሪያዎች ለማጠናከርና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል አበረታች ስራ መከናወኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለጹ፡፡ በክልሉ የሚገኙ ሆስፒታሎች የ2016 በጀት ዓመት ግምገማ እና የ2017 በጀት…

ሲዲሲ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ክትባትን ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) የዝንጀሮ ፈንጣጣ ክትባትን በቀናት ውስጥ ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ማዕከሉ ፥ በአህጉሪቱ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የተስፋፋባቸው ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት…

ከሕንድና አሜሪካ ለመጡ የሕክምና በጎ ፍቃደኞች የእውቅና መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የልብ ቀዶ ሕክምና እና ስልጠና ለሰጡ የሕንድ እና አሜሪካ በጎ ፍቃደኞች የእውቅና እና የምስጋና መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡ በመርሐ ግብሩ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ÷ኢትዮጵያ በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ፕሮግራም የጤና ሥርዓቱን ለማሻሻል…

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የመተላለፊያ መንገድና ምልክቶች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሁኑ ወቅት የዓለም የጤና ስጋት ተብሎ በዓለም ጤና ድርጅት የተፈረጀው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በዝንጀሮ በጂነስ ኦርቶፖክስ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተላላፊ ህመም ሲሆን÷ በሽታው ካለበት ሰው ወይም…

የአጥንት መሳሳት መከላከያ መንገዶች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአጥንት መሳሳት ህመም በተለያዩ ምክንያቶች የአጥንት ይዘትና ክብደት መቀነስ ሲያጋጥም የሚፈጠር ህመም ነው፡፡ የአጥንትና የመገጣጠሚያ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ጸጋ ይልማ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የአጥንት መሳሳት…

የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣን በሽታ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆኑን አወጀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት እየተስፋፋ ያለውን የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታን ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ሲል አውጇል፡፡ ቫይረሱ በኮንጎ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እየተስፋፋና ህጻናትና ጎልማሶች በበሽታው እየተያዙ መሆኑም ተሰምቷል፡፡…

በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው የለም – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው አለመኖሩን ጤና ሚኒስቴር አረጋገጠ፡፡ ዛሬ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ተቋም (አፍሪካ ሲ ዲ ሲ) ባወጣው መግለጫ÷ በ13 የአፍሪካ ሀገራት 2 ሺህ 863 ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ…