Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ስፓርት

ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምሽት 12፡00 ላይ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ። ለወላይታ ድቻ ፀጋዬ ብርሃኑ 45ኛ ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር ለንግድ ባንክ ደግሞ ኪቲካ ጅማ በ14 ደቂቃ ላይ ግብ…

ባህርዳር ከተማ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በተካሄደው የ19ኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ መርሃ ግብር ባህርዳር ከተማ ፋሲል ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ። ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ለባህርዳር ከተማ ቸርነት ጉግሳ በ46ኛው እና በ91ኛው…

ፊፋ የኮንጎ ሪፐብሊክንና የፓኪስታንን እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች አገደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የኮንጎ ሪፐብሊክን እና የፓኪስታንን እግር ኳስ ፌደሬሽኖች ማገዱ ተሰማ። የኮንጎ እግር ኳስ ማህበር (ፌኮፉት) ከዓለም አቀፍ እግር ኳስ ውድድሮች የታገደው በተቋሙ ውስጥ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ…

አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የግማሽ ማራቶን አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዱባይ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸናፊ ሆናለች። አትሌት ያለምዘርፍ 1 ስዓት ከ7ደቂቃ ከ09 ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት ማጠናቀቋን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል።

13ኛው የሀዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 13ኛው የሀዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ፡፡ 21ኪሎ ሜትር በሸፈነው በዚህ ውድድር በወንዶች አትሌት አስቻለው ብሩ ፣በሴቶች ደግሞ ምህረት ገመዳ አሸንፈዋል።…

በ800 ሜትር የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አትሌት ፅጌ ድጉማ ድል ቀናት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንሳይ ሜዝ በተካሄደ የ800 ሜትር የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ውድድር እትሌት ፅጌ ድጉማ አሸንፋለች፡፡ ፅጌ የ800 ሜትሩን 1 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ97 ማይክሮ ሴኮንድ በመጨረስ በቀዳሚነት ማጠናቀቋን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ…

ስሑል ሽረ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ጨዋታ ስሑል ሽረ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ። ምሽት 12፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም…

የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ኮከብ ማርሴሎ ጫማ ሰቀለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚላዊው የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ማርሴሎ ከእግር ኳስ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡ የግራ መስመር ተከላካዩ ማርሴሎ በሪያል ማድሪድ ቤት ስኬታማ ጊዜን ያሳለፈ ሲሆን 5 የሻምፒዮንስ ሊግ እና 6 የላሊጋ ዋንጫዎችን ከሎስ ብላንኮቹ ጋር…

የእግር ኳስ ንጉሱ የ40 ዓመታት ጉዞ..

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው የአል ናስር አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ረጅም የእግርኳስ ኮከብነቱን አስቀጥሎ በዛሬው እለት 40ኛ አመቱን ደፍኗል፡፡ በእግርኳስ አለም በርካታ ክዋከብቶች የተፈጠሩ ቢሆንም ክብራቸውን አስጠበቀው እና እስከ መጨረሻው የዓለም የእግር ኳስ…

በ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቼክ ሪፐብሊክ ኦስታርቫ ከተማ በተካሄደው የዓለም የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ አሸንፋለች፡፡ አትሌት ፍሬወይኒ የርቀቱን በ8 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ከ17 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ ነው ማሸነፍ የቻለችው፡፡ የ1 ሺህ…