Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
በሎስ አንጀለስ በተከሰተ ሰደድ እሳት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በተከሰተ ሰደድ እሳት 30 ሺህ ሰዎች አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መተላለፉ ተሰምቷል፡፡
ሰደድ እሳቱ በተከሰተ በሰዓታት ቆይታ ውስጥ ከ10 ሄክታር ወደ 2 ሺህ 900 ሄክታር መሬት መስፋፋቱ ተገልጿል፡፡…
በርዕደ መሬት የ95 ሰዎች ሕይዎት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ቻይና ቲቤት ግዛት 7 ነጥብ 1 ሬክታር ስኬል የተመዘገበ ርዕደ መሬት የ95 ሰዎችን ሕይዎት ሲቀጥፍ ከ130 በሚልቁት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡
ርዕደ መሬቱ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ጥልቀት እንዳለው እና ሺጋትሲ በተባለችው የቲቤት…
የፈረንሳይ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ከሙአመር ጋዳፊ ገንዘብ በመቀበል ወንጀል ተከሰሱ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳይ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ከሊቢያ የቀድሞ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ለምርጫ ቅስቀሳ 50 ሚሊየን ዩሮ ገንዘብ ተቀብለው ነበር የሚል ክስ ቀርቦባቸው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ፈረንሳይን ከፈረንጆቹ 2007 እስከ 2012 በፕሬዚዳንትነት…
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ተገደሉ
አዲስ አበባ፣ ታህሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡
የጋዛ ንጹሃን መከላከል ኤጀንሲ በጥቃቱ በከተማዋ የሚገኙ የመኖሪያ ህንጻዎች መውደማቸውን ጠቁሟል፡፡
በጥቃቱ ዙሪያ ከእስራኤል ወገን እስካሁን የተባለ…
በካሊፎርኒያ አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ሕይዎት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በካሊፎርኒያ ፉለርተን ከተማ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
አደጋውን ተከትሎ የፉለርተን ከተማ ፖሊስ በሰጠው ማብራሪያ÷ ከሞቱት በተጨማሪ በ18 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል፡፡
የአደጋው…
በቱኒዚያ በጀልባ መገልበጥ አደጋ የ27 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቱኒዚያ ምሥራቃዊ የባሕር ጠረፍ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ቢያንስ የ27 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
የመገልበጥ አደጋው በሁለት ጀልባዎች ላይ የደረሰ ሲሆን÷ ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 27…
ኤሎን መስክ የቴስላ ሳይበር መኪና ፍንዳታ የሽብር ተግባር ሊሆን እንደሚችል ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በላስ ቬጋስ ትራምፕ ሆቴል መግቢያ በር በቴስላ ሳይበር መኪና ላይ የተከሰተው ፍንዳታ የሽብር ተግባር ሊሆን እንደሚችል የዓለም ቁጥር አንድ ቱጃሩ ታዋቂው ባለሃብት ኤሎን መስክ ገለጸ፡፡
ትናንት በፈረንጆቹ አዲስ አመት የመጀመሪያ ቀን የተመራጩ…
በኒው ኦርሊያንስ ህዝብ ወደተሰበሰበት መኪና የነዳው ግለሰብ የ10 ሰዎች ህይወት ቀጠፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ኒው ኦርሊያንስ ህዝብ ወደተሰበሰበት መኪና የነዳው ግለሰብ የ10 ሰዎች ህይወት ቀጠፈ።
በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ 30 ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ተሰምቷል።
በኒው ኦርሊያንስ ቦርቦን ጎዳና ላይ የተከሰተው…
ዩክሬን ወደ አውሮፓ ሀገራት የሚተላለፈውን የሩሲያ ጋዝ አቋረጠች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዩክሬን በኩል ለአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሚቀርበው የሩሲያ ጋዝ በዩክሬን የጋዝ ማመላለሻ ኦፕሬተር ናፍቶጋዝና በሩሲያ ጋዝፕሮም መካከል ያለው የአምስት ዓመት ስምምነት ማብቃቱ ተሰምቷል፡፡
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ፥ በመሬታችን…
አሜሪካ የሁቲ አማጽያን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ጦር በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ የሁቲ አማጽያን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የአየር ጥቃት መሰንዘሩን አስታወቀ፡፡
ጦሩ በአማጽያኑ ወታደራዊ ማዘዣ፣ የጦር መሳሪያ ማከማቻ እና ፋብሪካ ላይ በርካታ የአየር ጥቃቶች መፈጸሙን አስታውቋል፡፡…