Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
በደቡብ ሱዳን በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
አውሮፕላኑ ከግዛቷ ተነስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በማቅናት ላይ እያለ መከስከሱን የግዛቱ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ጋትዌች ባይፓል መግለጻቸውን ሬውተርስ…
ዩክሬን የሩሲያ ነዳጅ ማጣሪያን በድሮን መታች
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዩክሬን በአንድ ሣምንት ውስጥ ሁለተኛውን የሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያ በአራት ሰው አልባ አውሮፕላኖች መምታቷ ተሰምቷል፡፡
ከምስራቅ ዩክሬን በ800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የሩሲያ ክስቶቮ ከተማ የሚገኘውን የነዳጅ ማጣሪያ መምታቷን ነው ዩክሬን…
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኋይት ሀውስ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ሊመክሩ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቅርቡ በዓለ ሲመታቸውን ፈጽመው ወደ ሥራ የገቡት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኋይት ሀውስ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ኔታኒያሁ ጋር ሊመክሩ መሆኑ ተነገረ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፤ ከፕሬዚዳንት…
በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ሃይል ለማመንጨት 35 ቢሊየን ዶላር ሊመደብ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ሌሎች ተቋማት በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ሃይል ለማስፋፋት ቢያንስ 35 ቢሊየን ዶላር ለመመደብ የሚያስችል ቃል መግባታቸው ተሰምቷል፡፡
በታንዛኒያ ዳሬሰላም ይህን አስመልክቶ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የዓለም…
ሩሲያ የካንሰር መከላከያ ክትባት ሙከራ ልታካሂድ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ የካንሰር መከላከያ ክትባት ሙከራ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት አጋማሽ ላይ እንደምታካሂድ አስታውቃለች፡፡
የሩሲያ ተመራማሪዎች ለበርካታ ዓመታት ሁሉንም የካንሰር ዓይነቶች ለመከላከል የሚውል ክትባት ለዓለም ለማበርከት ሲሰሩ መቆየታቸው…
በአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ የከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ የከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ በኬኒያ ናይሮቢ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ በተለይም በህብረቱ ዘላቂ ፋይናንስ እና የስራ መዋቅር ማሻሻያ እንዲሁም ህብረቱ…
በርካታ ፍልስጤማውያን ወደ ቀያቸው መመለስ ጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤል እና ሃማስ የደረሱትን ስምምነት ተከትሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ወደ ሰሜን ጋዛ ማቅናት ጀምረዋል፡፡
እስራኤል እና ሃማስ የደረሱት ታጋቾችን የመለዋወጥ ስምምነት ተከትሎ ነው ፍልስጤማውያኑ ተፈናቃዮች እስራኤል ተቆጣጥራው በነበረው…
የተባበሩት መንግስታት አሜሪካ በሚቀጥለው ዓመት ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት እንደምትወጣ አረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግስታት አሜሪካ በፈረንጆቹ 2026 ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት እንደምትወጣ አረጋግጧል።
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡…
ፕሬዚዳንት ፑቲን ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ክሬምሊን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ክሬምሊን አስታወቀ፡፡
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሩሲያ ከትራምፕ ጋር ለሚደረገው ውይይት የዋሽንግተንን ምላሽ…
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሁቲ አማጺያን በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ትዕዛዝ ሰጡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በየመን የሚገኙት የሁቲ አማጺያን በድጋሚ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በሰሜናዊ የመን የሚንቀሳቀሱት የሁቲ አማጺያን በውጭ የሽብር ቡድን መዝገብ ውስጥ እንዲካተቱ በሚያዘው ረቂቅ…