Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ  እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች  የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው- ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች  የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው  ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር)  ተናገሩ። የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ…

ከ28 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዐውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከመስከረም 18 እስከ 24/2017 ዓ/ም ከ28 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚቀርቡበት ዐውደ ርዕይ ሊካሄድ መሆኑን ገልጿል፡፡ ዐውደ ርዕዩ ሚኒስቴሩ ከደቡባዊ ትብብር ድርጅት ጋር በመተባበር…

ኅብረቱ እና ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ልማት የዓረብ ባንክ ለአኅጉሪቱ ዕድገት በጋራ እንደሚሠሩ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኅብረት እና ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ልማት የዓረብ ባንክ ለአኅጉሪቱ ዕድገት በአጋርነት እንደሚሠሩ አስታውቀዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የግማሽ ዓመት ግምገማ ጉባዔ በጋና አክራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ ከጉባዔው ጎን ለጎንም የአፍሪካ ኅብረት…

በጎፋ ዞን በመሬት ናዳ የተፈናቀሉትን ለመደገፍ ርብርብ ይደረጋል- አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በተከሰተ የመሬት ናዳ ምክንያት የተጎዱና የተፈናቀሉትን ለመደገፍ ርብርብ እንደሚደረግ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ አረጋገጡ፡፡ በተጨማሪም ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ተገቢው ጥንቃቄ…

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በሀገራዊ ስትራቲጂያዊ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ከተወያዩ በኋላ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡ ችግኝ ተከላው "ኢትዮጵያ ትተክላለች ትውልድ ያፀናል" በሚል…

በጎፋ ዞን በተከሰተ የመሬት ናዳ ከ20 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ዛሬ ረፋድ 4 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ አደጋ ከ20 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በተከሰተው አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ ከ20 በላይ አስከሬን…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በሚያዚያ ወር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በመገናኘት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ…

በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ከተሰማሩ የጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል በጣሊያን፣ ሮምና ሚላን ከሚኖሩ ዳያስፖራዎችና በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ከተሰማሩ የጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡ አቶ ረሻድ ከማል÷ ከኢትዮጵያዊያንና ትውልድ-ኢትዮጵያዊያን ጋር…

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሃላፊዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስናና በሃብት ምዝበራ ተጠርጥረው ነው። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ታምራት…

ሩሲያ 75 የዩክሬን ድሮኖችን ማውደሟን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ የአየር መከላከያ ዘዴ 75 የዩክሬን ድሮኖችን ማውደሙን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ከ75 ድሮኖች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሀገሪቱ ደቡብ ምዕራብ በምትገኘው ሮስቶቭ ግዛት ውስጥ መውደማቸውም ተጠቁሟል፡፡ ከዩክሬን…