የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጥለዋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በ35ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና በ40ኛዉ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ለመሳተፍ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጥለዋል።
በዚህም የኬንያ፣ የዩጋንዳ፣ ማላዊ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ የናሚቢያ፣ የኮሞሮስ፣ የብሩንዲና የሞዛምቢክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፕሮቶኮል ዋና ሹም አምባሳደር ፈይሰል አልይ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!