Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ለኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የከብት መኖ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ለኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የከብት መኖ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ የተደረገው በኦሮሚያ ክልል በጉጂ፣ ቦረና እና ባሌ አካባቢ በድርቅ ለተጎዱ አርብቶ አደሮች ነው።
ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የኦሮሚያ ክልል ምን ጊዜም ቢሆን ከአማራ ክልል ህዝብ ጋር በክፉም በደጉም አብሮ የኖረ ህዝብ ነው ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል የአማራ ክልል በትህነግ ቡድን ቅጣት በተቃጣበት ጊዜ ከጎን በመቆም አጋርነቱን አሳይቷል ፣ኢትዮጵያውያን በመፎካከር ሳይሆን በመተባበር ከችግር መውጣት እንደሚቻል አሳይቷልም ነው ያሉት።
መለያየት የትንሽነት ምልክት በመሆኑ ብልጽግናን አያረጋግጥምም ብለዋል ።
ድህነትን፣ስራ አጥነትንና የኑሮ ውድነትን ምላሽ የምንሰጠው ከተባበርን ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ ፥ የኦሮሚያክልል ህዝብ ሲቸገርና ሲጎዳ የአማራ ክልል ህዝብ ዝም አይልም በሚል ነው በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ አብሮነታችንን ለማሳየት ድጋፍ ያደረግነው ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳም በበኩላቸው፥ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፥ የአማራ ክልል ከፍተኛ ችግር ውስጥ ቢሆንም በክልላችን ለደረሰው ድርቅ ድጋፍ በማድረጉ በህዝባችን ስም እናመሰግናለን ብለዋል።
ለኢትዮጵያ አዋጪው መንገድ አንድ መሆን ነው ፣አሁንም የአማራና የኦሮሞ ህዝብ አንድ ህዝብ ነው፣አብረው መስዋትነት ከፍለዋል የትህነግ አላማም እንዳይሳካ አድርገዋል ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ።
ድርቅን ብቻ ሳይሆን ድህነትን በጋራ አሸንፈን ኢትዮጵያን በዕኑ እናቆማለንም ሲሉ ተናግረዋል።
በፈትያ አብደላ እና በዙፋን ካሳሁን
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.