Fana: At a Speed of Life!

የሞዛምቢክ ፣ የጂቡቲ እና የኬንያ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞዛምቢክ ፣ የጂቡቲ እና የኬንያ ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤን ለመታደም ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ኒዩሲ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ለመታደም ዛሬ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌህም በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በተመሳሳይ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ በሚጀምረው 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሌላ በኩል የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ፀሐፊ አሚና መሀመድ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ምክትል ፀሐፊዋ አዲስ አበባ አምባሳደር ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የካቢኔ ጉዳዮች ዋና ሹም አምባሳደር ምህረተዓብ ሙሉጌታ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ዮሴፍ ካሳዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪም በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ሹም አምባሳደር ፈይሰል አሊይ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአፍሪካ ህብረት 35ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬና ነገ ይካሄዳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.