የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ ህብረትን ሊቀመንበርነትን ተረከቡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ ህብረትን በሊቀመንበርነት የመምራት ሃላፊነቱን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ተረከቡ።
35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በህብረቱ ህገ ደንብ መሰረትም ሴኔጋል የወቅቱን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነት ቦታን ለአንድ ዓመት ይዛ ትቆያለች።
የህብረቱ የወቅቱን ሊመንበርነት የተረከቡት የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸው መክፈቻ የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ጨምሮ የተለያዩ ችግሮችን እየተጋፈጠች መሆኑን ተናግረዋል።
እነዚህ መሰናክሎችን ለማለፍም የአፍሪካ አገራት አንድ መሆንን የሚጠይቅ እንደሆነ አንስተው፥ ከሰላም እና ደህንነት ጋር ተያይዞ ሽብርተኝነትን መዋጋት፣ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ችግሮችን በዋነኛነት ጠቅሰዋል፡፡
አህጉራችን በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡
የመሪዎቹ ጉባኤው “የአፍሪካ አኅጉርን የሥርዓተ ምግብ አቅም በመገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ እና ነገ የሚካሄድ ይሆናል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!