ሀገር አቀፍ አስተማማኝ እናትነት ቀን በጅግጅጋ ከተማ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ጥር 30፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በየአመቱ ጥር 30 የሚከበረው ሀገር አቀፍ አስተማማኝ እናትነት ቀን ዛሬ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተከብሯል።
በሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ አዘጋጅነት “በጋራ ተባብረን በመስራት መከላከል የሚቻለውን የእናቶች ሞትን እንግታ “በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ አስተማማኝ የእናትነት ቀን ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ ከክልሉ ጤና ቢሮና ከተለያዩ የጤና ተቋማት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች ፣ የጤና ባለሞያዎች ፣ እናቶችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የአስተማማኝ እናትነት ቀን በየዓመቱ ጥር 30 በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበረት ሲሆን ፥ ለእናቶች በእርግዝናና በወሊድ ወቅት ተገቢውን የጤና አገልግሎቶችን በመስጠት የእናቶች ሞትን ማስወገድ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።
በበዓሉ ላይ የተገኙት በሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ የበሽታ መከለከልና ጤና ማበልፀግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዲ ፋራህ ፥ በክልሉና በሀገሪቱ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን በማሳደግ የእናቶች ሞትን ለማስወገድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በየዓመቱ የሚከበረው የአስተማማኝ እናትነት ቀን የእናቶች ሞትን በመቀነስ በኩል፣ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተባብሮ ለመስራት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር የገለፁት ዳይሬክተሩ፥ የጤና ባለሞያዎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል።
በሥነ ስርዓቱ ላይ ስለ አስተማማኝ እናትነት ፣ በክልሉና በሀገሪቱ የእናቶች የሞት ሁኔታ ፣ በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት የእናቶች የጤና አገልግሎት አጠቃቀም ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎችና በዘርፉ የሚታዩ ችግሮች እንዲሁም የእናቶችን የጤና አጠቃቀምን ለማጠናከር በተቀመጡ የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ያተኮረ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ እናቶችና የጤና ባለሞያዎች የአስተማማኝ እናትነት ቀን እናቶች በእርግዝናና በወሊድ ወቅት በጤና ተቋማት በተገቢው መንገድ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ያስችላል ማለታቸውን ከክልሉ ብዙሃን መገናኛ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!