የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እና የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ 1 ቢሊየን ዶላር ብድር ማግኘት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እና የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (አፍሪ ኤግዚም ባንክ) ለኢትዮጵያ ባንኮች 1 ቢሊየን ዶላር ብድር ማግኘት የሚያስችል ስምምነት ተፊራረሙ።
ስምምነቱ በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮችን የሚያግዝ የ1 ቢሊየን ዶላር ብድር ማግኘት የሚያስችል መሆኑን የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ተናግረዋል።
ስምምነቱ የንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎችን ማገዝ የሚያስችልም እንደሆነም ተገልጿል።
ይህ የብድር ስምምነት በሃገሪቱ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመፍታት እና ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ትልቅ ጠቀሜታ ያለው እንደሆነም የባንኩ ገዢ ገልጸዋል።
በዚህ የስምምነት ፊርማ ላይ የብድሩ ተጠቃሚ የሚሆኑ የግል ባንክ ተወካዮችም ተገኝተዋል።
በይስማው አደራው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!