የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከሀላፊነት አነሱ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሀላፊነት አነሱ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሄንሪ-ማሪ ዶንድራን ከስልጣናቸው የተሰናበቱት በሀገሪቱ መንግስት ውስጥ የሩሲያ እና የፈረንሣይ ደጋፊ በሚል በተፈጠሩ ቡድኖች መካከል ካለው ውጥረት ጋር ተያይዞ መሆኑ ነው የተነገረው።
በተሰናበቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ምትክም በኢኮኖሚ ሚኒስትርነት ሲያገለግሉ በነበሩት ፊሊክስ ሞላዋ መተካታቸውን የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
እንደ ቲ አር ቲ ዘገባ ሄንሪ-ማሪ ዶንድራን ጠቅላይ ሚኒስትር ተብለው የተሰየሙት በፈረንጆች 2021 ነበር። በአቋማቸው ለፈረንሳይ ቅርበት እንዳላቸው ይነገራል።
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ቆይተው ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላም ነው የማባረር እርምጃውን የወሰዱት ተብሏል።
ባለፉት አራት ዓመታት በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሩሲያ ተፅእኖ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፥ በሞስኮ ወታደራዊ ድጋፍ የሀገሪቱ መንግስት በአማፂያን እጅ የነበረ ሰፊ ቦታን ነፃ ማድረግ ችሏል።
ለፈረንሳይ ቅርብ መሆናቸው የሚነገርላቸው ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ጋር ጥሩ ቅርበት አላቸው በሚልም ነበር የተሾሙት።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!