ከሊባኖስ 149 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ከሀገሪቱ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ጋር በመነጋገር በተለያየ ምክንያት ያለ ህጋዊ ሰነድ በሊባኖስ ይኖሩ የነበሩ 149 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ገልጿል።
በተመሳሳይ ከ149 በተጨማሪ በሊባኖስ ያለሠነድ ይኖሩ የነበሩ 61 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
የተመለሱት ዜጎች በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር ተመዝግበው የነበሩ መሆናቸውንም ቆንስላ ጀነራል ጽህፈት ቤቱ ማስታወቁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽኅፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!