Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት ስዋሂሊን የስራ ቋንቋ እንዲሆን የቀረበለትን ጥያቄ አፀደቀ

አዲስ አበባ፤የካቲት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የአፍሪካ ህብረት ሰዋሂሊ የስራ ቋንቋው እንዲሆን የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል፡፡
ውሳኔዉ የፀደቀዉ የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ምፓንጎ ለአፍሪካ ህብረት ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ፕሬዚዳንቱ ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ ተካሄዶ በነበረው 35ኛው የአፍሪካ ኅብረት ስበሰባ ላይ፥ ሰዋሂሊ ቋንቋ በአፍሪካ ከ100 ሚሊየን በላይ ተናጋሪዎች እንዳሉት አንስተው ነበር።
ስለሆነም በአፍሪካ አህጉር በስፋት ከሚነገሩ ቋንቋዎች አንዱ በመሆኑ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ሀሳብ ማቅረባቸው ተመላክቷል፡፡
ቀደም ብሎም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የአፍሪካ ኅብረት ስዋሂሊ የፓን አፍሪካ ቋንቋ እንዲሆን ግፊት ሲያደርጉ መቆየታቸዉ ተገልጿል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥናት መሰረት ቋንቋው መነሻው ምስራቅ አፍሪካ ሲሆን፥ በአሁኑ ሰዓት በ14 ሀገራት ማለትም በታንዛኒያ፣ኬንያ፣ኡጋንዳ፣ሩዋንዳ፣ብሩንዲ፣ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሞዛምቢክ ፣ ማላዊ ፣ ዛምቢያ ፣ ኮሞሮስ እና በመካከለኛው ምስራቅ እስከ ኦማን እና የመን ድረስ እየተነገረ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.