የኦሮሚያና የጋምቤላ ክልሎች በልማትና በሠላም ላይ ለመሥራት የሚያስችል የስምምነት ሠነድ ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያና የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ርዕሳነ-መስተዳድሮች በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በልማትና ሠላም ማስፈን ላይ በጥምረት ለመሥራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ናቸው፡፡
ስምምነቱ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሸኔ እና በመሰል ጀሌዎቹ ሊፈጽም የሚያቅደውን የተለመደ የሽብር ተግባር ለማምከን ያስችላል፤ በልማትም ክልሎቹን ያስተሳስራል ነው የተባለው፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ ወደ ጋምቤላ ክልል ማቅናታቸውን እና የኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውንም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጽህፈት ቤት መግለጹ ይታወሳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!