Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይት መድረክ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ ላይ ነው፡፡

የመድብለ ፓርቲ ግንባታ ፣ ምርጫ እና ምርጫ ነክ ጉዳዮች ፣ ሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ፣ የህግ የበላይነት እና የህግ አስፈጻሚ አካላት፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ የሀገረ መንግስት  ምስረታ፣ የመልካም አስተዳደር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች  ላይ ነው የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ምክክር በማካሄድ ላይ የሚገኙት።

በፓርቲዎች ይቀርቡ የነበሩ አቤቱታዎችን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማጣራቱን አስታውቆ ፣የተጣራውን ሪፖርት ማቅረብም የውይይቱ አካል ሆኖ በአጀንዳነት ተይዟል ።

በምክክር መድረኩ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ  ብርቱካን ሚዴቅሳን ጨምሮ ሌሎች የቦርዱ አመራሮች እና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ በመድረኩ እንደገለጹት፥ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን አቤቱታ የሚመለከት አጣሪ ቡድን በመቋቋም ሁለት ጊዜ አጣርቶ ውጤቱን ለፓርቲዎቹ አቅርቧል።
ዛሬ የቀረበው ሪፖርትም በክልሎች እና በፓርቲዎች ተለይቶ የቀረበ መሆኑን አሳውቀዋል።
በዚህም በፖለቲካ ተሳትፏቸው ምክንያት የታሰሩ፣ የተፈቱ፣ የተፈረደባቸው፣ ጉዳያቸው በሂደት ላይ ያለ የፓርቲ ሰዎች ጉዳይ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም ቀርበዋል።
ፓርቲዎቹ የሚጠበቅባቸውን ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ እና ሰነዶችን አሻሽሎ መቅረብ ጋር በተያያዘም ችግሮች እንዳሉ ተነስቷል። በመሆኑም እንደ አፋር ክልል ያሉ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ማስገባት ተገቢ መሆኑን የጠቆሙት የቦርዱ ሰብሳቢ፥ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህግ የተቀመጠውን አሰራር ማክበርና ማሟላት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በለይኩን ዓለም

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.