Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ግማሽ ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፀድቅ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ 500 ሚልየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፀደቅ ውሳኔ አሳለፈ።
ተጨማሪ በጀቱ በሚቀጥሉት ወራት ለድርቅ አደጋው ምላሽ የሚውል መሆኑ ተገልጿል። በተለይም ለተለያዩ ምግቦች መግዣ፣ ለውሃ፣ ለጤናና ለእንሰሳት መኖ አቅርቦት የሚመደብ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም ካቢኔው በተለያዩ ደንቦችና ረቂቅ አዋጆች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ ለክልሉ ምክር ቤት መምራቱን ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ካቢኔው ያፀደቀው ተጨማሪ በጀት፣ ደንቦችና አዋጆች ቅዳሜ የክልሉ ምክር ቤት በሚያደርገው ጉባኤ ከፀደቀ በኋላ ተግባራዊ እንደሚሆን የሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ረሺድ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.