በነቀምቴ 18 ኪሎ ግራም እጢ ከአንዲት ወጣት በቀዶ ሕክምና ተወገደ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በነቀምቴ ከተማ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል 18 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ከአንዲት 22 ዓመት ወጣት በቀዶ ሕክምና ማስወገዱን ገለጸ።
ታካሚዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ ነዋሪ ስትሆን ፥ በተለያዩ ጤና ተቋማት ሕክምና ስትከታተል መቆየቷ ተገልጿል።
በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር አምሳሉ ታከለ የተመራ የዶክተሮች ቡድንም ለወጣቷ የተሳካ ቀዶ ሕክምና አከናውኗል፡፡
በዚህም 18 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ከወጣቷ በቀዶ ሕክምና ማስወገድ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
ታካሚዋ በአሁኑ ሰዓት በሙሉ ጤንነት ላይ እንደምትገኝም ተጠቁሟል፡፡
በገላና ተስፋ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!