Fana: At a Speed of Life!

በግንቦት ወር ከ135 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በግንቦት ወር 135 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ።

በተጨማሪም 348 የቱርክ ስሪት ሽጉጥ እና 300 ጥይት መያዙን አስታውቀዋል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በሁሉም የሀገሪቱ የጉምሩክ ጣቢያዎች በተደረገው ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ መያዛቸውን ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

ሥራውን በተገቢው ሁኔታ በመሥራት አስተዋፅኦ ላደረጉ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች እና የጸጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ሚኒስትሩ የቁጥጥርና ክትትል ሥራው አድካሚ፣ ውስብስብና ከባድ ቢሆንም የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.