የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ም/ቤት 6ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባዔው ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን÷ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ጉባዔው የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅም ተጠቁሟል።
በተጨማሪም የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የዋና ኦዲት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2017 ዕቅድ ላይ ተወያይቶ የሚያጸድቅ መሆኑ ተገልጿል።
ጉባዔው የክልሉን የ2017 በጀትና ሌሎች ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።