የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በሀገራዊ ስትራቲጂያዊ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ከተወያዩ በኋላ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
ችግኝ ተከላው “ኢትዮጵያ ትተክላለች ትውልድ ያፀናል” በሚል መሪ ሐሳብ የተጀመረው የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚሁ ወቅት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ለአንድ አካል የሚተው ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በቀጣይም በሀገራዊ የልማት መርሐ-ግብሮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።