Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ካቢኔ የ2017 በጀት ከ40 ቢሊየን ብር በላይ እንዲሆን የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል የ2017 በጀት ዓመት የክልሉ በጀት 40 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ እንዲፀድቅ የክልሉ ካቢኔ የውሳኔ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

ካቢኔው ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የክልሉ የ2017 በጀት ዓመት በጀት 40 ቢሊየን 687 ሚሊየን 127 ሺህ 7 ብር እንዲሆን በማጽደቅ ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል፡፡

የበጀቱ 43 በመቶ በክልሉ ገቢ ቀሪው 57 በመቶ በፌዴራል መንግሥት ድጎማ የሚሸፈን መሆኑ ተገልጿል።

ለ2017 የቀረበው ረቂቅ በጀት ከ2016 በጀት ጋር ሲነፃፀር የ6 በመቶ ብልጫ እንዳለው መገለጹን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.