Fana: At a Speed of Life!

ብልጽግና ፓርቲ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ትናንት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት በሰው ሕይወት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡

ፓርቲው ባወጣው የሐዘን መግለጫ÷ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የበኩሉን እንደሚወጣም አረጋግጧል፡፡

የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ማርቆስ መለሰ በበኩላቸው የአስቸኳይ አደጋ ጊዜ መልሶ ማቋቋሚያ ኮሚቴ ተቋቁሞ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

አሁንም የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን በመግለጽ እስከ አሁን ባለው መረጃ የሟቾች ቁጥር 157 መድረሱን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.