Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 17 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2017 በጀት ዓመት 17 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ።

የቀረበው በጀት ከክልል ገቢ የሚሰበሰብ፣ ከፌዴራል መንግስት ድጎማና ከሌሎች የገቢ ምንጮች የሚገኝ መሆኑን ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ለክልል ማዕከል መ/ቤቶች መደበኛና የካፒታል ወጪ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን፣ ለዞኖች ጥቅል በጀት 14 ነጥብ 5 ቢሊየን፣ ለክልላዊ ፕሮግራሞች 995 ነጥብ 6 ሚሊየን፣ ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 434 ነጥብ 7 ሚሊየን፣ ለክልሉ መጠባበቂያ በጀት 120 ሚሊየን በአጠቃላይ 17 ቢሊየን 622 ሚሊየን 88 ሺህ 402 ብር ሆኖ መጽደቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.