ምክር ቤቱ በሙስና የተጠረጠሩ የአንድ የም/ቤት አባልን ያለ መከሰስ መብት አነሳ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ የምክር ቤት አባልን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሔደ ነው።
በጉባዔው አቶ መዚድ ራህመቶ በሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው ምክር ቤቱ ያለ መከሰስ መብታቸውን ማንሳቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡