የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለ2017 በጀት አመት ከ33 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ከ33 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ አጽድቋል።
ምክር ቤቱ ባካሄደው 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ2ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ነው ለ2017 በጀት ዓመት 33 ቢሊየን 652 ሚሊየን 116 ሺህ 26 ብር በጀት ያጸደቀው፡፡
በጀቱ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ32 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡
የበጀቱ ምንጭ ከውስጥ ገቢ፣ ከፌዴራል መንግስት ከሚሰጥ ድጎማና ከሌሎች የገቢ ምንጮች ነው መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡