የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡና ንብረት ለወደመባቸው ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል፡፡
አገልግሎቱ ለተጎጂ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና ለአካባቢው ነዋሪዎችም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተመላክቷል፡፡