የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የ20 ሚሊየን ብር እድለኛውን ሸለመ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የ20 ሚሊየን ብር እድለኛውን ሸልሟል፡፡
ጳጉሜን አምስት ቀን እጣው የወጣው እንቁጣጣሽ ሎተሪ አሸናፊን ነው አገልግሎቱ የሸለመው።
የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አንደኛ እጣ አሸናፊ መምህር አስረሳኸኝ ጌታቸው በአገልግሎቱ በመገኘት 20 ሚሊየን ብሩን ተረክበዋል።
የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቤዛ ግርማ÷ አገልግሎቱ በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ በመሆን በርካቶችን እድለኛ እያደረገ ነው ብለዋል።
አቶ አስረሳኸኝ የዩኒቨርሲቲ መምህር ሲሆኑ÷ ሎተሪ በተደጋጋሚ ይቆርጡ እንደነበር ተናግረዋል።
ጉዞ ላይ የቆረጡት የእንቁጣጣሽ ሎተሪ የ20 ሚሊየን ብር እድለኛ እንዳደረጋቸው የተናገሩት ባለእድለኛው በኪራይ ቤት እንደሚኖሩና ገንዘቡ ህይወታቸውን እንደሚቀይርላቸውም ገልጸዋል።
በቅድስት አባተ