Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት የግብርና ግብዓት በማቅረብ የኢኮኖሚ መዋቅሩን በማስተካከል ረገድ እየሠራ ነው- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት የግብርና ግብዓት በማቅረብ የኢኮኖሚ መዋቅሩን በማስተካከል እና የንግድ ሥርዓቱን በማመቻቸት ረገድ በስፋት እየሠራ እንደሚገኝ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

አቶ ሽመልስ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ÷ የለውጡ መንግሥት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር፣ የክልሉን የኢኮኖሚ መዋቅር ዝንፈት ለማረቅና ያለን ትልቁ አቅም ግብርና መሆኑን ተገንዘቦ ነው ወደ ሥራ የገባው ብለዋል፡፡

የስንዴ ልማት ላይ እየታየ ያለው ክንውን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ የሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ግብዓት በማስፋት እና ወጪ ንግድን በመጨመር ረገድ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ጅምሩን ለማስፈንጠር መንግሥት የግብርና ግብዓት እና ቴክኖሎጂ በማቅረብ፣ የአርሶ አደሩን ክህሎት በማሳደግ፣ የኢኮኖሚ መዋቅሩን በማስተካከል እና የንግድ ሥርዓቱን በማመቻቸት ረገድ በስፋት እየሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

የሴክተሩን ሁለንተናዊ ሽግግር እውን በማድረግ የወል እና የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ፣ በግብርናው ዘርፍ መውሰድ የጀመርናቸውን ስትራቴጂካዊና የተቀናጁ ርምጃዎች አጠናክረን መቀጠል እንዳለብን በየደረጃው ያለ አመራር የሚስተው ጉዳይ አይደለም ሲሉም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.