የኢትዮጵያና አልጄሪያን ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና አልጄሪያን ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአልጄሪያው አቻቸው አሕመድ አታፍ ጋር በሩሲያ ሶቺ እየተካሄደ ከሚገኘው የመጀመሪያው የሩሲያ አፍሪካ የሚኒስትሮች አጋርነት ፎረም ጎን ለጎን ተወያተዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማሳደግ በተለያዩ የትብብር ዘርፎች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
በኢትዮጵያ እና በአልጄሪያ መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲሁም በአህጉራዊ የጋራ ጉዳዮች ላይም መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡