Fana: At a Speed of Life!

የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም ያለመ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም እና በቴክኒክ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት ያለመ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ኤስ ጂ አውቶሞቲቭ ግሩፕ እና ሚስተር ሉታ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ናቸው፡፡

ስምምነቱ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋትና የኃይል አቅርቦቱ ተደራሽነት ላይ በጋራ ለመሥራት ያለመ መሆኑን የግሩፑ መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚሁ መሠረት የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም እና በቴክኒክ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት ያለመ ሲሆን÷ የመኪና ቻርጅ ማድረጊያዎች ግንባታንም ስምምነቱ ማካተቱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የመግባቢያ ስምምነቱ ገበያ ላይ አብሮ ለመሥራት እንደሚያስችል እና በዚህም ገበያውን እስከ ምስራቅ አፍሪካ ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.