Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው እድገት አስደናቂ ነው – ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበችው እድገት አስደናቂ መሆኑን ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን በ15ኛው የሩሲያ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር፥ አፍሪካ እና ሩሲያ ስላላቸው የጠበቀ ግንኙነት ገለጻ አድርገዋል፡፡

በዚህም አፍሪካ ቅርባችን እና አስተማማኝ አጋር ናት፤ ከአህጉሪቱ ህዝብ ጋርም ብዙ ግንኙነት አለን ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በዓለም አቀፍ እና በምዕራባውያን የባለሙያዎች ግምገማ መሰረት አፍሪካ ጥሩ የእድገት ተስፋዎች እንዳሏት ይጠቁማሉ ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከዚህ ጋር ተያይዞ ባነሱት ሃሳብ የአንዳንድ ሀገራት ኢኮኖሚዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ እያደገ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለአብነትም ኢትዮጵያን ባለፉት ዓመታት በምሳሌነት የሚጠቀስ ዕድገት ማስመዝገቧን አንስተዋል፡፡

እንደ ፑቲን ገለጻ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ 120 በመቶ የሆነ ዕድገት ማስመዝገቧን ጠቅሰው ይህም አስደናቂ ነው ማለታቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.