Fana: At a Speed of Life!

ከዩክሬን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ሳይሆን ዘላቂ ሰላም ያስፈልጋል – ቭላድሚር ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ሳይሆን ዘላቂ ሰላም ያስፈልጋል ሲሉ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ለተነሳላቸው ከ70 በላይ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠታቸውም ተገልጿል።

በዚሁም ስለሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትና አሁናዊ ሁኔታ ያብራሩት ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሁለት ዓመት ተኩል የዘለቀው የዩክሬን ግጭት እንደ ሰው ጉዳቱ እንደሚሰማቸው ገልጸዋል፡፡

“ጦርነቱ ለሁላችንም ማለትም ለሀገሬና ለእኔ ፈታኝ ነው” ሲሉ ገልጸው፣ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለመሸማገል ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡ ሆኖም ዩክሬንም በተመሳሳይ ዝግጁ ልትሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡

ፑቲን ቀደም ሲል ዩክሬናውያን እና ሩሲያውያን ወንድማማች ህዝቦች መሆናቸውን እንዲሁም ሞስኮ የኪዬቭ መንግስት አገዛዝን ብቻ በጠላትነት እንደምትፈርጀውም ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የሩሲያ ዜጋ ለመሆን ለሚፈልጉ የውጭ ዜጎች ቅድሚያ ስለሚሰጠው ፖሊሲ ሲያብራሩ ከዩክሬናውያን ለሚቀርበው የዜግነት ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጠውም አመላክተዋል።

በዚህም ዩክሬናውያን በባህል የሚመስሉን ናቸው ሲሉ መግለጻቸውን የዘገበው አር ቲ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.