በአመቱ ወደ ስፔን ለመሻገር የሞከሩ ከ10 ሺህ በላይ ስደተኞች መሞታቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ 2024 ከአፍሪካ ወደ ስፔን ለመሻገር የሞከሩ 10 ሺህ 457 ስደተኞች ባህር ውስጥ ሰምጠው መሞታቸው የስደተኞች መብት ቡድን አስታወቀ።
ካሚናንዶስ ፍሮንቴራስ የተባለው የስደተኞች መብት ቡድን ባወጣው ሪፖርት÷ ከሟቾች ውስጥ 1 ሺህ 588 ህጻናትና 421 ሴቶች እንደሚገኙበት ጠቅሷል።
በዚህም በየቀኑ በአማካኝ 30 ስደተኞች መሞታቸውን የጠቀሰው የቡድኑ ሪፖርት የሟቾቹ ቁጥር ከዓምናው ጋር ሲነጻጸር 58 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል።
ብዙዎቹ ስደተኞች መነሻቸው ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ሌሎቹ ስደተኞች ከሞሪታኒያ በጀልባዎች ወደ ስፔን ለመሻገር ሲሞክሩ ህይዎታቸው ያለፈ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ ታህሣሥ 15 ቀን 2024 ድረስ ብቻ ከ57 ሺህ 700 በላይ ስደተኞች ከሞሪታኒያ ተነስተው ስፔን መግባታቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።
የስፔን መንግስት በፈረንጆቹ የካቲት 2024 ላይ ለሞሪታኒያ መንግስት ህገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎችንና ከሀገሪቱ ጠረፍ የሚነሱ ጀልባዎችን ለመቆጣጠር የሚውል 218 ሚሊየን ዶላር እርዳታ መስጠቱ በዘገባው ተጠቅሷል።