Fana: At a Speed of Life!

ናሳ ለፀሐይ ቅርብ በሆነ ርቀት መንኮራኩር ማሳለፍ መቻሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ጣቢያ (ናሳ) ፓርከር ሶላር ፕሮብ ለፀሐይ ቅርብ በሆነ ርቀት መንኮራኩር ለማሳለፍ ያደረገው ጥረት መሳካቱን አስታውቋል፡፡

ናሳ መንኮራኩሩ ከጸሃይ በቅርብ ካለፈ በኋላ “ደህንነቱ የተጠበቀ” መሆኑን እና የተሳካ ተልዕኮ ማድረጉን ገልጿል፡፡

በጸሃይ ጎን በሚያልፍበት ወቅት ከምድር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ያልነበረው መንኮራኩሩ ትናንት ከእኩለ ሌሊት በፊት ከናሳ ጋር ግንኙነት ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡

የተልዕኮው መሳካት የፀሐይ ንፋስ አመጣጥን እንዲሁም በፀሐይ ወደ ምድር በሚለቀቁ ቅንጣቶች ላይ ሳይንስቶች የተሻለ መረዳት እንዲኖራቸው ያደርጋል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የጠፈር መንኮራኩሩ በሰዓት 430 ሺህ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን ከፍተኛ ሙቀትን እና ጨረሮችን መቋቋም አንዲችል ተደርጎ መሰራቱም ተገልጿል፡፡

እስከዛሬ ከተደረጉት ሙከራዎች አሁን ላይ የተሳካው ሙከራ ለፀሐይ የቀረበ መሆኑም ተነግሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.